YeneTech.com
14/03/2025
ሚዲያ እና የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በቅርበበት ለመስራት እንዲያችል ምክክር ተካሄደ፡፡
የምክክር መድረኩ"የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚዲያ ድርሻ የላቀ ነው" በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት የቢሮው አማካሪ ዶክተር ታደለ ደመኮ፤ ቢሮው በከተማ አስተዳደር ከሚገኙ 50 በላይ ቢሮዎች በተለየ መልኩ በሰው ልጆች ላይ አትኩሮ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
የሴቶችን ተጠቃሚነት እና ተደራሽነት እንዲሁም ክንውኑ ምን ይመስል ነበር የሚሉትን ከ ሰፊ ማብራሪያ ጋር ሰተዋል ለሚዲያዎች፡፡ወደ ፊትም በይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና ተጨባጭ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚቻልም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
እንዲሁም ቢሮው ከሰው ልጆች ፅንስት እስከ ግብዓት መሬት ድረስ እንደሚሰራ ገልፀው፤ በ2017 ግማሽ በጀት ዓመት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ጥረቶች መደረጋቸውን ተናግረዋል።
እንደ ዶክተር ታደለ ገለፃ በዚህ በመዲናይቱ በግማሽ በጀት ዓመቱ ከተፈጠረው 142ሺህ የስራ ዕድሎች 52 በመቶ ሴቶች ናቸው።
ከለውጥ በዋላ በሴቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ በመስራቱ በተጨባጭ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጠ እየተቻለ መሆኑን ያነሱት የቢሮው አማካሪው፤ በሴቶች ላይ የሚስተዋለውን አይችሉም የሚለውን ኋላ ቀር ትርክት በይችላሉ መቀየር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለነገ የማይባል ነው ብለዋል።
ሚዲያ ለማጥፋትም ሆነ ለማልማት ሚናው የጎላ እንደሆነ በመግለፅ፤ የሚዲያ ባለሞያዎች ለሴቶች ድምፅ ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
እስካሁን በነበረው ሂደት የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሚዲያዎች ለሚያደርጉት ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።
በመዲናይቱ ሴቶች በሰላም ማስከበር፣ በፅዳት፣ በአከባቢ ጥበቃ፣ በበጎ ፍቃድ፣ በደም ልገሳና ሌሎች ዋጋቸው በማይተመኑ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
የድምፃዊ መሳይ ተፈራ -ደህና ይግጠምሽ በተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ፡፡
04/01/2025
ማስታወቅያ…
A🎤O የሳውንድ ሲስተም ኪራይ
የድሮ VHS ወደ ፍላሽ እንገለብጣለን:: እናንተ ብቻ ይደውሉ በተጨማሪም ለፕሮፌሽናል ሳውንድ ኢንጅነሪንግ ብቻ የሚያገለግል Cable Tester በቀላሉ ኬብላችሁን ችግሩን የምታውቁበት ቴስተር ነው ይከራዩ ስራዎን በቅልጥፍና ይስሩ፡፡
ከድሮ VHS📼 ወደ ፍላሽ እንገለብጣለን
B- 0911-643422 P-0911-225086
የካሊንባ ዩትዮብ ስፖንሰር ስለሆነ እናመሰግናለን፡፡
22/12/2024
ከፍያለ ጌጡ…
እስካሁን ካየኃቸው ቱባዊ የባህላዊ የሙዚቃ አቀንቃኞች መሀከል እጅጉኑ ይለይብኛል፡፡ በፋና ላምሮት ቤት… ውበትም ጌጥም ሆኖ እስከ አስራ ሁለተኛ ሳምንት ድረስ ተጉዟል፡፡በዚህኛው በአስራ ስምንተኛው ምዕራፍ የተለየ የሙዚቃ አቀራረብ እና አጨዋወት አሳይቶናል፡፡
*ቱባዊ ቃና ድምፅ(ፎክ)
የትም የማይገኝ መለዮ ቃና…ለጥቂቶች ብቻ የሚታደል ውበታዊ ሀገራዊ አንፀባራቂዎች ናቸው፡፡ለሌሎች ፈተናን የሆነ የሙዚቃ ቴክኒክ አጠቃቀም በቀላሉ ሳይቸገር አስደንቆ እንድንማርበት ያደርገናል፡፡ከፍያለ ጌጡ… በጊዜ የተስዕጦን መንገድ ያወቀ እና የነቃ ነው፡፡ ከቀዬው ያወቃቸውን የሚያውቃቸው የሙዚቃ ቃና እና ባህልን ፋንትው አድርጎ በቴሌቪዥን መስኮት አስመልክቶናል፡፡
*የመድረክ ዝግጅት እና አቀራረብ…
የውድድር አንዱ ፈተና የመድረክ ዝግጅት ነው… በራስ መተማመን እንድንለካው የመጣንበትን የሙዚቃ አቀራረብ ይሄ ነው ያለኝ ብለን የምንገልፅበት ትልቁ መድረካችን ነው፡፡ከፍ ያለ ይንን አስመልክቶናል፡፡በአለባበስ፣በእንቅስቃሴ፣ የተለያዩ የሙዚቃ ምርጫ ስኬት፣ የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋቾች ጋር ውህደትን የመሳሰሉት ይታያሉ፡፡
*ለየት ያሉ የሙዚቃ ምርጫዎች
ይንን ስገልፅላችሁ በቀላል አትመልከቱት ሙዚቃ መምረጥ ሌላ… የሙረጡትን ሙዚቃ መጫወት ሌላ ነው፡፡ እነዚህ ሁለትን አዛምዶ ማዜም አንዱ የውድድር መልክ ናቸው፡፡ከፍ ያለ ጌጡ ልንሰማቸው የሚገቡ በብዛት በመድረክ የማንሰማውን አስደምጦናል ለምሳሌ ወሮታው ውበት ፣ተስፋዬ ውቤ ፣ይሁኔ በላይ ፣ቻላቸው አሸናፊ እና የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡
በፋና ላምሮት ቤት ብዙ እድሎች ይገኛሉ አንደኛውም ለአምስተኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ላይ በሰርፕራይዝ(ድንቴ ደስታ) ተፈጥሮ፡፡ ከፍ ያለን እምንመለከተው ይመስለኛል፡፡መልካም እድል ይሁንልህ ጓዴ፡፡
የሙዚቃ ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Selam Chuna Tesfaye Lemlem Yohannes Miheret Yoseph Natnael Sisay Girum Nebiyu
Click here to claim your Sponsored Listing.