ZaB
አሁን ይሄ ትዝታ ነው ወይስ ቂም 🤔🤔🤔 ምንድነው እያለ ያለው?
ZaB follow this page for more information
14/05/2026
🇨🇳 ቻይና ዶናልድ ትራምፕን በድጋሚ በዓለም ፊት አዋረደች‼️
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው ዕለት በቻይና ለሚያደርጉት ጉብኝት ቤይጂንግ ሲደርሱ፡ የቻይናው ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ ሊቀበሏቸው ወደ አውሮፕላን ማረፊያው ሳይሄዱ ቀርተዋል።
በርካታ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች፡ ቻይና ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ቀይ ምንጣፍ አንጥፋ በፕሬዝዳንቷ አማካኝነት ደማቅ አቀባበል እንደምታደርግላቸው በጉጉት ሲጠባበቁ የነበረ ቢሆንም፡ ነገር ግን ጉብኝቱ ገና ከጅምሩ የትራምፕን ቆሌ የገፈፈ ሆኗል።
አቀባበሉ ፕሬዚዳንታዊ አቀባበል መሆን ሲገባው፡ ይልቁንም ለትራምፕ አቀባበል ያደረጉለት በሚያሳዝን መልኩ በቻይና የአሜሪካ አምባሳደር ዴቪድ ፔርዱን ጨምሮ የፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ምክትል የሆኑት ሃን ዜንግ፣ በዋሽንግተን የቻይና አምባሳደር ሼይ ፌንግ እና እንዲሁም በሚኒስትር ደኤታ ደረጃ ላይ የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች መሆናቸው ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
ZaB follow for mor
13/05/2026
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና በርካታ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚዎችን አስከትለው ወደ ቻይና አቀኑ። ትራምፕ እና የቻይና አቻቸው ሺ ዢንፒንግ ሐሙስ እና አርብ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ስብሰባ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ የሚካሔደው በኢራን ጦርነት የኢነርጂ ዋጋ በከተኛ መጠን ባሻቀበበት ወቅት ነው። የአሜሪካ እና የቻይና የንግድ ልውውጥ እና የአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው።
በአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ቀዳሚ የሆኑ የአሜሪካ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚዎች ከዶናልድት ትራምፕ ጋር ወደ ቻይና አቅንተዋል። ለአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ቁልፍ ግብዓት የሆኑ ቺፖች በማምረት የሚታወቀው የንቪዲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀንሰን ሑዋንግ፣ የአፕል ሥራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ እና የቴስላው ኤለን ሙስክ ከልዑካን ቡድኑ መካከል ይገኙበታል።
በቤጂንግ በሚደረገው የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ አሜሪካ ለታይዋን የምትሸጠው የጦር መሣሪያ ጉዳይ ከሺ ዢንፒንግ እንደሚነጋገሩ ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ብለው አሳውቀዋል። የቻይና ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ግን ታይዋን የቻይና አንድ አካል በመሆኑ አሜሪካ የሚኖራትን ወታደራዊ ግንኙነትም ይሁን ከዚህ ቀደም የተስማማቸውን የጦር መሣሪያ ሽያጭ አጥብቀው ተቃውመዋል። ባለፈው ታኅሳስ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር 11 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የጦር መሣሪያዎች ለታይዋን እንደሚሸጥ ይፋ አድርጎ ነበር።
ZaB like this page
12/05/2026
🇪🇹
አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ገቡ።
ዛሬ ምሽት የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አዲስ አበባ ገብተዋል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለዋና ጸኃፊው አቀባበል አድርገዋል።
ZaB like and follow this page for more
12/05/2026
በዲላ ከተማ የ6 ዓመት ሕፃን አግተው የተሰወሩ ተከሳሾች እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ።
በዲላ ከተማ የ6 ዓመት ሕፃን ልጅ አግተው በመሰወርና ገንዘብ በመጠየቅ ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች፣ በዲላ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ።
ተከሳሾቹ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ብሩክ ወልደኪዳን የተባለ ሕፃንን አግተው ወደ ሲዳማ ክልል በመውሰድ ከቤተሰቦቹ ጋር በገንዘብ ሲደራደሩ የነበረ ቢሆንም፣ በፖሊስ በተደረገ ጥብቅ ክትትል ከነታጋቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የዲላ ከተማ ፖሊስ መምሪያና ዐቃቤ ሕግ በጋራ ባቀረቡት ክስ መሠረት፣ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ 1ኛ ተከሳሽ እንዳሻው በቀለን በ12 ዓመት እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ ጌቱ ገረመውን በ9 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።
በተጨማሪም ተከሳሾቹ በድርድር ወቅት በባንክ ተላልፎላቸው የነበረው 80 ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ ለሕፃኑ አባት ለአቶ ወልደኪዳን ባንታ እንዲመለስላቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የዲላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ተወካይ ረዳት ኢንስፔክተር ጴጥሮስ ዘለቀ እንደገለጹት፣ ወንጀሉ ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ "በብሔራዊ ደህንነት መረጃና በፀጥታ አካላት የተቀናጀ ኦፕሬሽን ሕፃኑን በሰላም ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀል ተችሏል" ተብሏል።
ZaB Follow, like and share the page for more
Click here to claim your Sponsored Listing.