HUDA

HUDA

Share

01/03/2025

❤የአድዋ ድል ሲታሰብ የኢትዮጵያ የታሪክ አርማ ሸዋ

✍ሸዋ ደብረ ብርሃን ንጉሡና ፈላስፈው አጼ ዘርዐ ያእቆብ የመሰረታት ከተማ ናት
✍ሸዋ ደብረ ብርሃን በአሰራሩ ግሩም የሆነው የደብረ ብርሃን ስላሤ ቤተ ክርስቲያን የሚገኝበት የታሪክ ምድርነው
✍ሸዋ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ወደኢትዮጵያ እንዲመጣ መንፈሳዊ ስራ የሰሩት የአጼ ዳዊት ምድር ነው
✍ሸዋ መስቀለ ክርስቶስን ወደኢትዮጵያ አምጥቶ በበግሸን መስቀለኛ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ያደረገ እና በርካታ የሃይማኖት የፍልስፍና የምርምር የታሪክ መጻሕፍትን የጻፈና ከሀድያንን ድል የነሳው የኢትዮጵያው ንጉሥ የአጼ ዘርዐ ያእቆብ የልደት ቦታ ነው
✍ሸዋ ቡልጋ በጸሎቱ ክንፍ ያወጣው ጻድቅ የአቡነ ተክለሃይማኖት መገኛ ምድር ነው
✍ሸዋ ቡልጋ በጸሎቷ በምናኔ ህይወቷ ልዩ የሆነችሁ እና ክንፍ ያወጣችሁ የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ የትውልድ ቦታ ነው
✍ሸዋ ተአምረኛው መዘዞ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኝበት ቦታ ነው
✍ሸዋ ድንቅ ድንቅ ተአምራት የሚከናወኑበት ጠገሮ እጨጌ ዮሐንስ ገዳም የሚገኝበት ቅዱስ ምድር ነው
✍ሸዋ የኢትዮጵያውያን የሕመም ችገር የሚፈታበት የታመሙት ሁሉ ተጠምቀው የሚድኑበት ሸንኮራ ዮሐንስ የሚገኝበት ቅዱስ ቦታ ነው
✍ሸዋ ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበት ሳማ ሰንበት ያለበት የተቀደሰ ስፍራ ነው
✍ሸዋ የፈላስፈው ባለ ቅኔ ሊቁ ኢያሱ መገናኛ ነው
✍ሸዋ የጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነው ነጩ ጣሊያንን ደባቅ መቶ የአፍሪካን ነጻነት የኢትዮጵያን ድል ያቀዳጀው ዳግማዊ ሚኒሊክ ምድር ነው
✍ሸዋ ለኢትዮጵያ ስልጣኔ መነሻ የሆነ ባቡር መብራት መኪና ስልክ ወዘተርፈ ወደኢትዮጵያ ያመጠው የሚኒሊክ የትውልድ ቦታ ነው
✍ሸዋ ተአምር በማድረጓ በፈዋሽ ጸበሏ የምትታወቀው ጻድቃኔ ማርያም ገዳም የምትገኝበት ምድር ነው
✍ሸዋ የየኔታ ቤተ የአቋቋም ምስክር የነበረበት ኤልሻማ መድኃኔዓለም መገኛ ነው
✍ሸዋ የታላቁና ተአምር አድራጊው ዘብር ገብርኤል የሚገኝበት የተአምራት ቦታ ነው
✍ሸዋ ስዕለት ሰሚዋ ኩኬለሽ ማርያም ያለችበት ቦታ ነው
✍ሸዋ የቅዱሳን አጽም የማይፈርስበት የመልከ ጼዴቅ ገዳም የሚገኝበት ቅዱስ ምድር ነው
✍ሸዋ ቅዱስ ኡራኤል ደሙን የረጨበት ጽዋ የሚገኝበት እመጓ ኡራኤል ያለበት ድንቅ ምድር ነው
✍ሸዋ በዲንጋይ ላይ ዘንባባ የታተመባት ልዩና አስደናቂ የሆነችሁ ጅሩ ኣርሴማ ያለችበት ቅዱስ ምድር ነው
✍ሸዋ ልዩ ልዩ ገዳማትና አድባራት የድንጋይ ፍልፍል ቤተ መቅደሶችና የዋሻ ገዳማት የሚገኙበት አስገራሚ ቦታ ነው
✍ሸዋ ምንጃር ኤራቡርቲ 44 ታቦታት በአንድ ላይ የሚወርዱበት በታቦታት የተቀደሰ ምድር ነው
✍ሸዋ የተጉለቴ ዜማ መፍለቂያ ምድር ነው
✍ሸዋ የህይወት ምግብ የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማሳተም የትውልዱን ዓይነ ልቡና ያበሩ ተስፋ ገብረ ስላሤ የተወለዱበት ምድር ነው
✍ሸዋ የበርካታ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ሊቃውንት መፍለቂያ ምድር ነው
✍ሸዋ የታላቁ የደጉ አባት የብጹእ አቡነ ኤፍሬም የትውልድ ቦታ ነው
✍ሸዋ በሀገረ መንግስት ግንባታ
በኪነ ህንጻ
በገዳማት ኣድባራት ምስረታ
በስነ ጽሑፍ ስራዎች
ለኢትዮጵያ የታሪክ ሰንደቅ ነው
✍በዘመናችንም የስነ ጽሁፎ ሰዎች
ሀገር ወዳድ ሰዎች የጥበብ ሰዎች የአቋም ሰዎች የሚገኙበት ምድር ነው
ብቻ ሸዋ ደብረ ብርሃን የኢትዮጵያ የታሪክ ሰንደቅ ነው
የኢትዮጵያ የድል የታሪክ ኣርማ ሸዋ ነው
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ

28/02/2025

አንድ ባቡር ጣቢያ ለአንዲት ተማሪ ሲል ለዓመታት በኪሳራ ሲሰራ ኖሯል፡፡

ካሚ ሺራታኪ ባቡር ጣቢያ ነው፡፡ በጃፓን ሆካይዶ በተሰኘች ከተማ ይገኛል፡፡ ይህ ባቡር ጣቢያ የተሳፋሪ ቁጥር በጣም ሲያሽቆለቁልበትና የሚጠቀመው ሰው ሲያጣ ከሚከስር ይዘጋ የሚል ሃሳብ ቀረበ፡፡ የባቡር ጣቢያው ሃላፊዎች ጥናት ሲያደርጉ አንዲት ተማሪ ብቻ ወደትምህርት ቤቷ ለመሄድና ለመመለስ በየቀኑ ይህንን ባቡር ጣቢያ እንደምትጠቀም ታወቀ፡፡

ባለስልጣናቱ ጣቢያውን ከመዝጋት ይልቅ አንድ አስደናቂ ውሳኔ አሳለፉ፡፡ ጣቢያው ልጅቷ ትምህርቷን እስክታጠናቅቅ ድረስ ስራውን እንዲቀጥል ወሰኑ፡፡ ለብዙ ዓመታት ባቡሩ ሳይዛነፍ በሰዓቱ እየመጣ ወደትምህርት ቤት የምትሄደውን ልጅ ማሳፈርና ከትምህርት ቤቷ ስትመለስ በሰዓቱ እየደረሰ ወደቤቷ የመመለስ አገልግሎቱን መስጠት ቀጠለ፡፡ ልጅቷ ትምህርት መጨረሷ ሲረጋገጥ ባቡር ጣቢያው እስከወዲያኛው ተዘጋ፡፡

ይህ ድርጊት አሁን ድረስ በዓለም ላይ የሃላፊነት ምሳሌ እና ለትምህርት የተደረገ ክብር መግለጫ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡

በጣም ስትሰለጥን እንዲህ ነው የምታስበው!!

(መላኩ ብርሃኑ)

ለ አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎች
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/Hulumereja123

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Adis Abebea
Addis Ababa
1974