EthioPulse

EthioPulse

Share

Photos from EthioPulse's post 28/09/2025

ቡታጅራ ምን ተፈጠረ❓❓
ከትናንት መስከረም 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ በቡታጀራ ከተማ ግጭት ተቀስቅሷል።
የግጭቱ ምክንያት ደሞ ለዘመናት በመስቃን ወረዳ እንቦር ቀበሌ ይተዳደርበት የነበረው የስናኖ ሴራ የዞኑ አስፈፃሚዎች ስናኖ ሴራ የእንቦር ቀበሌ አደለም የዶቢ ቀበሌ ነው ብለው በመወሰናቸው እና ዛሬ በመስቃን ወረዳ ዋና ከተማ ቡታጀራ ሴራና አዳራሽ ላይ ዝግጅት በማዘጋጀታቸው የተነሳ ሲሆን ይህም በተደጋጋሚ የመስቃን ወጣቶች ሽማግሌዎች ይሄ ልክ አደለም "ባህል የማጥፋት ተልዕኮ ነው " ብለው የመስቃን ወጣቶች ትናንት ምሽት መስከረም 17/2018 ዓ.ም ጀምረው በቡታጅራ ከተማ ወደ አደባባይ ወጥተው የተቃውሞ አመፅ ማንሳታቸውን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
በከተማዋ ሆቴሎች፣መኪኖች እና መገልገያ ንብረቶች ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
ዛሬም ድረስ አመፁ የቀጠለ ሲሆን በከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል ብለዋል።
ችግሮች በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ይልመድብን።

( #ኢትዮፐልስ)
===================
💎⬇️⬇️⬇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
Telegram
Telegram

Photos from EthioPulse's post 26/08/2025

🚨 ‎የሰሜን ኮርያ ሁለንተናዊ መሪ ኪም ወታደሮቻቸው ከሀገር አልፈው በሩሲያና ዩክሬንና ምዕራባውያን ጦርነት ላይ ታላቅ ጀብድ እየፈፀሙ መሆናቸውን የምዕራባውያን የበላይነት ለማስቆምና ሁለቱ ሀገራት ፍትሃዊ አለም ለመፍጠር እየሰሩ እንደሆነ መናገራቸው ተሰማ ።

‎የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሰራዊቱ የባህር ማዶ ኦፕሬሽን መኮንኖች ጋር ባደረጉት ውይይት የሰሜን ኮርያ ወታደሮች ከራሳቸው አልፈው ሩሲያ ከዩክሬንና አጋሮቿ ጋር በምታደርገው ጦርነት የሀገራቸውን ጦር ታላላቅ ድሎችን እያስመዘገቡ በተሰማራበት አዉደ ዉጊያ በድል ላይ ድል እየተቀዳጀ መሆኑን አሞካሽተው ማመስገናቸዉን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግቧል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

‎ኪም በሩሲያ ኩርስክ ክልል ውስጥ ለሚያገለግሉት መኮንኖች እና ወታደሮች "ሞቅ ያለ ማበረታቻ ሰጥቷል" ፒዮንግያንግም የምዕራባውያን ተስፋፊነት የኔቶን ወወራ ለማስቆም ለሩሲያ እንዲዋጉ ከ10,000 በላይ ተዋጊዎችን እንደላከችም መሪዋ ተናግረዋል
‎ሲል የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት (KCNA) ሐሙስ ዕለት ዘግቧል።

‎ኪም በመዲናይቱ ላሉ ወታደራዊ አባላት ባደረጉት ንግግር በሩሲያ ታላቅ ድሎችን እያስመዘገበ የሚገኘዉ "የእኛ ጀግና ሰራዊት ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።

‎በኤፕሪል ወር ለመጀመሪያ ጊዜ ወታደሮቿን ከሩሲያ ወታደሮች ጋር ለመዋጋት ወደ ጦር ግንባር ማሰማራቷን የገለፁት ኩም ሰራዊታችን አሁን ማድረግ የሚገባውንና መደረግ ያለበትን እየሰራ ነው።ወደ ፊትም ያደርጋል። ብለዋል ።

‎ይህ በኪም እና በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ የተፈራረሙትን የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ተከትሎ የጋራ መከላከያ ስምምነትንም አካል ሲሆን ከዚህ በኋላ ሰሜን ኮርያን የሚነካ ማንኛዉ ሀገር ከሩሲያ ጋር በቀጥታ ወደጦርነት እንደሚገባ ማሳያ ነዉ ተብሏል ።

‎የኪም አስተያየት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩስያ እና የዩክሬን ጦርነት እንዲያበቃ ግፊት ባደረጉበት ወቅት መሆኑንና ፑቲን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ለኪም ማሳወቃቸዉ ደግሞ ከሁለቱም ሀገራት መሪዎች ምን ያህል በተቀናጀ መልኩ አብረው እንደሚሰሩ ማረጋገጫ ተደርጓል ለዚህም ማሳያ ባለፈው ሳምንት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሰሜን ኮሪያን ወታደሮች “ጀግና” ሲሉ ማሞገሳቸዉና የሩሲያና ሰሜን ኮርያ ግኑኝነት መቼም የማይናወጥ መሆኑን መግለፃቸው ማረጋገጫ ተደርጓል ።

‎የደቡብ ኮሪያ እና የምዕራቡ ዓለም የስለላ ኤጀንሲዎች ፒዮንግያንግ በ2026 ተጨማሪ ከ10,000 በላይ ወታደሮችን ከመድፈኛ ዛጎሎች፣ ሚሳኤሎች እና የረዥም ርቀት ሮኬቶች ጋር ወደ ሩሲያ ኩርስክ ክልል እንደምትልክ አስታውቀዋል። እስካሁንም ለሩሲያ ሲዋጉ ወደ 600 የሚጠጉ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለዋል በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል ሲል ሴኡል ተናግሯል ሲል [አልጀዚራ] ዘግቧል።

በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች አፈና፣ የዘፈቀደ እስራት እና ስወራ እንዳሳሰበው ሲፒጄ አስታወቀ - Addis standard 26/08/2025

ዜና: በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች አፈና፣ የዘፈቀደ እስራት እና ስወራ እንዳሳሰበው #ሲፒጄ አስታወቀ

የዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ ዮናስ አማረ መታፈኑን፣ የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ከድር መሐመድ ኢስማኤል በዘፈቀደ መታሰሩን እንዲሁም የአሐዱ ሬዲዮ 94.3 “ቅዳሜ ገበያ” ፕሮግራም አዘጋጁ አብዱልሰመድ መሐመድ የት እንዳለ ሳይታወቅ መቆየቱ ስጋት እንደፈጠረበት አስታወቀ።

የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ትናንት ረቡዕ ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የጋዜጠኞቹን ሁኔታ በዝርዝር አስቀምጧል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ለፌዴራል እና ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እንዲሁም ለሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያቀረባቸው ጥያቄዎች መልስ አለማግኘታቸውን ጠቁሟል።

የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ሙቶኪ ሙሞ “ኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ላይ አሳሳቢ ሪከርድ” እንዳላት እንዲሁም “ለጋዜጠኞች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስቸጋሪ እየሆነች መምጣቷን” ጠቁመው ባለሥልጣናት ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ያለበትን እንዲያጣሩ፣ ጋዜጠኛ ከድር እና ጋዜጠኛ አብዱልሰመድን በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች አፈና፣ የዘፈቀደ እስራት እና ስወራ እንዳሳሰበው ሲፒጄ አስታወቀ - Addis standard አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15/ 2017 ዓ/ም፦ የዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ ዮናስ አማረ መታፈኑን፣ የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ከድር መሐመድ .....

Photos from EthioPulse's post 25/08/2025

በየዓመቱ 250,000 ኢትዮጵያውያን እንደሚሰደዱ ሲገለጽ፤ ህገወጥ ስደትም አሳሳቢ ሆኗል።

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስደት የተለመደውን ትምህርት ላይ መሰረት ያደረገ የህይወት መንገድ በመተካት ላይ ይገኛል።

ምንም እንኳን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በሁሉም የትምህርት ደረጃ የትምህርት ተደራሽነት ቢስፋፋም አብዛኞቹ ተመራቂዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ስራ ለማግኘት ይፈተናሉ።

70 በመቶ ህዝቧ ከ30 አመት በታች በሆነችው ኢትዮጵያ የከተማ የወጣቶች የስራ አጥነት ምጣኔ በ2022 25.3 በመቶ ነበር።

ከኢትዮጵያ በየአመቱ ታዲያ ከ250,000 በላይ ሰወች ከሃገር ይሰደዳሉ ሲባል መደበኛ ያልሆነ ስደትም የብዙሃንን ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል።

ሰዎች እንዲሰደዱ የሚያደርጉ ምክንያቶች

ከ2000ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ ወደ ባህረ ሰላጤው ሃገራት መጓዝ ሲችሉ የአብዛኞቹ መዳረሻም ሳዑዲ አረቢያ ነበረች።

ከ2013-2018 ኢትዮጵያ በነዚህ ሃገራት የሚሰሩ ዜጎች እየሞቱ መሆኑን ተከትሎ በጊዜያዊነት ሰዎች ለስራ ወደነዚህ ሃገራት እንዳያመሩ እገዳ አስቀምጣ ነበር። በነዚህ ጊዜያትም በርካታ ሰዎች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሃገር ይወጡ ነበር።

በቂ የስራ ዕድል አለማግኘት፣ ግጭቶች እና አለመረጋጋት፣ በውጪ ሄዶ የተሻለ ኑሮን ለመኖር መመኘት፣ ቢዝነስ የመጀመር መንገዶች ውስንነት ሰዎች ስደትን የሚመርጡባቸው ምክንያቶች ናቸው።

በአንዳንድ የሃገሪቱ አካባቢዎች ደግሞ ስደት እንደ አጭርና ምርጡ የገቢ ማግኛ መንገድ ተደርጎ ሲወሰድ ውጪ ሃገር ዘመድ ያለው ሰውም ይከበራል የሚል ባህል አለ።

ሌላኛው ምክንያት በአማራ፣ ኦሮሚያ እንደዚሁም ትግራይ ክልል ያሉና የነበሩ ግጭቶች ወጣቶች መረጋጋትን ለማግኘት ስደትን እንዲመርጡ ሲገፋፋ ወጣቶቹ በጦርነት ወቅት ያላቸው ምርጫ ማቆሚያ አልባውን ጦርነት መቀላቀል አሊያም መሰደድ ነው።

በተጨማሪነት የሚነሳው ሌላኛው ምክንያት የኢትዮጵያ መንግስት በህጋዊ መንገድ ለመውጣት የሚያስፈልጉ ህጎችን ጠንካራ ማድረጉ ነው።

ለምሳሌ እንደ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ የትምህርት ደረጃ ወዘተ ያሉ ነገሮች ከሃገር መውጣት የሚፈልጉ ሰዎች በቀላሉ ሊያሟላቸው የሚችሏቸው ነገሮቸ አይደሉም።

ከፓስፖርት ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮች በራሱ አብዛኛው በቀላሉ ሊያሳካው የሚችለው ጉዳይ ስላልሆነ በህገወጥ መንገድ መሰደድን እንዲመርጡ ያደርጋል።

ሌላኛው ጉዳይ በህጋዊ መንገድ መሄድ ቢፈልጉ ጥቂት ዕድሎችን ብቻ ማግኘታቸው ነው። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር የተፈራረመቻቸው ስምምነቶች የስራ ዕድልን የሚያቀርቡት በብዛት ሴቶች የሚሳተፉባቸው ለቤት ውስጥ ስራ መሆኑ የወንዶቹን እና የቤት ውስጥ ስራዎችን መስራት ለማይፈልጉት ምርጫቸውን ይገድባል።

የስደት መንገዶች

የመጀመሪያው በምስራቅ ያለው ሲሆን ይህም የቀይ ባህርን በመሻገር በየመን አድርጎ ሳዑዲ አረቢያ መግባት ነው።

ከ2014 ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ76 ሺህ በላይ ስደተኞች ሲሞቱ 1098 ያህሉ የሞቱት በዚህ መንገድ ወደ የመን ለመግባት ሲሞክሩ በባህር ውስጥ ሰጥመው ነው።

በ2021 የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት እንዳስታወቀው ከተጠቀሰው አመት በፊት በነበሩ 5 አመታት ከሃገር የወጡ 51 ሺህ ኢትዮጵያውያን የገቡበት አልታወቀም።

ሁለተኛው ደግሞ የደቡብ መንገድ ሲሆን ይህም ከደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ተነስተው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚሄዱ ናቸው

ይህ መንገድ ሁለተኛው ትልቁ የህገወጥ የስደት መንገድ ሲሆን ሶስተኛው መንገድ በሱዳን፣ ሊቢያ እና ሜድትራንያን ባህር አድርገው አውሮፓ የሚገቡ ናቸው።

ምን አይነት የመፍትሄ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል ?

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከየትኛውም ጊዜ በላይ የኢኮኖሚ ዕድሎችን መፍጠር ሲጠበቅባት መንግሰትም የሙያ እና የስራ ፈጠራወችን በገጠራማው አካባቢ መደገፍ ይኖርበታል።

ሁለተኛው ህጋዊ የመሄጃ መንገዶች ማስፋፋት ነው። ይህም ከተለያዩ ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በማድረግ ሊጠናከር ይገባል። እነዚህ ስምምቶቸ ሲደረጉ ወጣቶች ሊሰሩባቸው የሚችሉ የስራ ዘርፎችን ማካተትም ይገባል።

ህጋዊ ከሃገር የመውጫ መንገዶችንም ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ እና መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ እንዲወስኑ ትምህርቶችን መስጠትም ያስፈልጋል።

በተጨማሪ ሙያን መሰረት ያደረጉ ትምህርቶች እና የስራ ዕድሎች መመቻቸት ይኖርባቸዋል።

[ የዚህ ጹሑፍ ዋናው ቅጂ በThe Conversation ላይ ማግኘት የሚቻል ሲሆን ጹሑፉ የዶ/ር ግርማቸው አዱኛ ነው። ]

Want your business to be the top-listed Media Company in Adama?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Adama
0000