Muhammad Tiqa Harar
01/04/2021
ሲገለጽ!
#ያለንበት ጊዜ የአፍሪካ ቀንድ በቀውስ ውስጥ ያለበት፣ ብዙ የየራሳቸው ፍላጎትና ዓላማ ያላቸው ኃይሎች የሚራኮቱበት፣ ውስብስብ መጠላለፍ በቀጠናው ያለበት ወቅት ነው። በዚያው ልክ ደግሞ በደም፤ በባህል፣ በቋንቋ እና በረጅም ጊዜ የጋራ ታሪክ የተሳሰርን ሕዝቦች ያለንበት አካባቢ ነው የውጭ ግንኙነታችንን በተመለከተ ሀገራችን የፓን አፍሪካኒዝም መሰረት፣ የአፍሪካ ህብረት መስራችና መቀመጫ፣ የቀድምት ዓለምአቀፍ ተቋማት መስራችና በአለም አቀፍ፤ በአህጉር አቀፍ እንዲሁም ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ጉልህና ገንቢ ሚና የምትጫወት ሀገር ናት። ይህንኑ በጋራ ተጠቃሚነትና እኩልነት ላይ የተመሰረተውን ፖሊሲያችንን አጠናክረን እንቀጥላለን። ከአፍሪካዊያን ወንድሞቻችን ወንድሞቻችን ጋር በአጠቃላይ፤ እና ከጎረቤቶቻችን ጋር በተለይ በችግርም በተድላም አብረን እንቆማለን። ከኤርትራ መንግሥት ጋር ለአመታት ሰፍኖ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃም ከልብ እንፈልጋለን። የበኩላችንንም እንወጣለን። በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለት ሀገር ሕዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል ልዩነቶቻችንን በውይይት ለመፍታት ያለንን ዝግጁነት እየገለለጽኩ የኤርትራ መንግሥትም ተመሳሳይ አቋም እንዲወስዱ በዚሁ አጋጣማ ጥሪዬን አቀርባለሁ!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Adama