Dawaa Aada Waada

Dawaa Aada Waada

Share

25/12/2024

#ቡግር (Acne) 𝗦𝗵𝗶𝗳𝗶𝗻𝗶𝗶𝗻𝗮

ይህ ህመም በፊት ላይ ከሚገኙ አነስተኛ ነጫጭ እና ጥቋቁር ነጥብጣቦች እስከ ሁሉንም የሰውነት ክፍል እስከሚያዳርስ መግል የቋጠሩ እብጠት ይደርሳል።

• ምንም እንኳ እስከሞት የሚያደርስ ችግር ባይሆንም የሰውነት ቆዳን በማበላሸት የስነ ልቦና ችግር ፣ ድብርት ፣ በራስ መተማመንን ይቀንሳል እንዲሁም የረጅም ጊዜ የቆዳ ለምጥ ያስከትላል ።
• 80% በሚሆኑ ሰዎች ላይ ቀለል ያለ ሰሆን 20% የሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድ ቡግር ይኖራቸዋል ።

👉ማንን ያጠቃል
• ምንም እንኳ በየትኛውም የእድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም በብዛት በአስራዎቹ እድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን በብዛት ያጠቃል ።
• ይህም በጉርምስና እና ኮረዳነት ጊዜ በሚጀመረው የሆርሞን በከፍተኛ መጠን መመረት ጋር የተያያዘ ነው።
• ከ14-30 ዓመት 80% የሚሆኑ ሰዎችን ሲያጠቃ ከ30-40 ዓመት 15% የሚሆኑ ሰዎችን ያጠቃል ።

👉እንዴት ይከሰታል

• በሰውነታችን ላይ ትንንሽ ቀዳዳዎች ሲኖሩ እነዚህ ቀዳዳዎች ከስራቸው ፀጉር ሊበቅልበት የሚችልበት ከመሆኑ በተጨማሪ በስራቸው የሚገኙትን የወዝ ዕጢዎች የሚያመርቱት ወዝ ወደ ላይኛው የቆዳ ክፍል የሚወጡበት ሲሆን ይህ ቀዳዳ ከመጠን በላይ በሆነ ስብ መመረት እና በሞቱ የቆዳ ሴሎች በሚደፈኑበት ጊዜ በሰውነታችን ላይ የሚገኝ ኩኒባክቴሪየም አክኒ ውስጥ ላይ እንዲራባ እና ቁስለት እንዲፈጠር ያደርጋል ።

👉የሚያጋልጡ ሁኔታዎች

• ለቡግር በዋናነት የሚያጋልጠው የዘረ-መል ሲሆን ይህም በቤተሰብ በብዛት እንዲገኝ ያደርገዋል ።
• ከሆርሞን ጋር የተያያዘ ይህም በአስራዎቹ እድሜ የመብዛት እና በወር አበባ ጊዜ የመጨመር ሁኔታ ያሳያል
• ከፍተኛ የሆነ የሆነ የወዝ መመረት
• የሰውነት የቆዳ ሴሎች የመመረት እና የመወገድ ሁኔታ አለመመጣጠን
• ሰውነት ላይ የሚደረጉ እንደ የጀርባ ሻንጣ፣ እራስ ላይ የሚደረጉ ኮፍያዎች እና ጥምጣም ፣ የጡጥ ማስያዣ ፣ ሄልሜት የመሳሰሉት የውዝ መውጫውን በመድፈን !

የትኛውን የሰውነት ክፍል ያጠቃል ?

• ቡግር በብዛት የፀጉር መውጫ ቀዳዳዎች በሚገኙበት ቦታ ማለትም በፊት ፣ በደረት አካባቢ እና በጀርባ ላይ ቢገኝም በሁሉም የሰውነት ቆዳ ላይ ሊወጣ ይችላል።

አይነቶቹ
• አነስተኛ ቡግር በቁጥር ከ30 በታች የሚሆኑ ነጫጭ እና ጥቋቁር ነጠብጣቦች
• መካከለኛ ቡግር በቁጥር ከ100 በታች የሆኑ ነጫጭ እና ጥቋቁር ነጠብጣቦች እና ቀያይ እብጠቶች
• ከፍተኛ ቡግር ተለቅ ያሉ ጠጣር ህመም ያላቸው እብጠቶች እና ህመም ያላቸው መግል የያዙ ከቆዳ ስር ያሉ እባጮች የያዘ

ምልክቶች
👉ነጭ አናት ያላቸው ነጠብጣቦች
👉ጥቁር አናት ያላቸው ነጠብጣቦች
👉ትናንሽ ቀያይ ህመም ያላቸው ነጠብጣቦች
👉ቀያይ ጫፍ ላይ ትንሽ መግል ያላቸው ነጠብጣቦች
👉ተለቅ ያሉ ጠጣር ህመም ያላቸው እብጠቶች
👉 ህመም ያላቸው መግል የያዙ ከቆዳ ስር ያሉ እባጮች

👉 ከእነዚህ ቆዳ ላይ ከሚታዩት ምልክቶች በተጨማሪ ከበድ ባሉ የቡግር አይነቶች ትኩሳት ፣ ብርድ ብርድ ማለት እና የመገጣጠሚያ ህመም ሊኖር ይችላል ።

👉 መፍትሄውስ..?
ቀጣዩ ጥያቄያ መሆኑ የሚጠበቅ ነው፡፡
👉 እነሁ👇
ለነፃ የማማከር አገልግልት ጭምር
ዋዳ ባህላዊ ህክምና መዕከል
𝗗𝗮𝘄𝗮𝗮 𝗔𝗮𝗱𝗮 𝗪𝗮𝗮𝗱𝗮 ያማክሩ ፔጁን ላይክ 👍 ማድረጎን አይርሱ
ለበለጠ መረጃ 📞+251912175505

Want your business to be the top-listed Media Company in Adama?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Adama