Abrehot Library

Abrehot Library

Share

Photos from Abrehot Library's post 28/05/2026

ርዕስ፦ ምንትዋብ
ደራሲ፦ ህይወት ተፈራ
የገጽ ብዛት፦ 270
የኅትመት ዘመን፦ 2012 ዓ.ም.
አድራሻ (ለአንባቢያን)፦ በአብርሆት ቤተ መጽሐፍት፣ 4ኛ ፎቅ፣ የልቦለድ ክፍል ይገኛል

አጭር ገለፃ

በደራሲ ሕይወት ተፈራ የተዘጋጀው "ምንትዋብ" የተሰኘው ታሪካዊ ልብወለድ መጽሐፍ፣ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩትን ጠንካራዋን መሪ እቴጌ ምንትዋብን ታሪክ መሠረት ያደረገ ነው። እቴጌ ምንትዋብ የአፄ በካፋ ባለቤት ሲሆኑ፣ ከባላቸው ሞት በኋላ የልጃቸውንና የልጅ ልጃቸውን አልጋ ወራሾች በሞግዚትነት በመምራት ለ40 ዓመታት አገሪቱን አስተዳድረዋል። በዘመናቸው በጎንደርና በጣና ሐይቅ ላይ የገነቧቸውና ያደሷቸው አብያተ ክርስቲያናት፣ የነበራቸውን የዲፕሎማሲ ችሎታ፣ እንዲሁም ለኪነ-ሕንጻና ለሥነ-ሥዕል የነበራቸውን ከፍተኛ ፍቅር መጽሐፉ ያሳያል። መጽሐፉ እውነተኛ ታሪካዊ ሰዎችን (እንደ እቴጌ ምንትዋብ) ‘ጥላዬ’ ከተባሉ በፈጠራ ከተጨመሩ ምናባዊ ገጸ-ባህሪያት ጋር በማስተሳሰር ፣ የእቴጌይቱን ሰውኛ ማንነትና የወቅቱን የሥነ-ሥዕል ትምህርትና ሥርዓት አጉልቶ ያሳያል።

በአጠቃላይ መጽሐፉ በስፋት ያልተወሳላቸውን የእቴጌ ምንትዋብን ታሪክ የሚተርክ ነው ይህም ለተቋማት ግንባታ፣ ለሥነ-ጥበብ ዕድገት፣ ለባለቅኔዎችና ለሰዓሊዎች "ክብር" በመስጠት ሥራዎቻቸው በተቋማዊ መልኩ እንዲቀርቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን።

Photos from Abrehot Library's post 25/05/2026

የልምድ ልውውጥ እና ስልጠና በአብርሆት! ✨📚

የአብርሆት ቤተመጻሕፍት ከ«ነገ ሌላ ቀን ነው» ተቋም ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የልምድ ልውውጥ እና የስልጠና መርሃ-ግብር በአብርሆት ቤተመጻሕፍት አከናውኗል። በዕለቱ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት ባለሙያዎች ለ«ነገ ሌላ ቀን ነው» ተቋም አባላት ሰፊና ጠቃሚ ስልጠና ሰጥተዋል። በስልጠናውም፦
የቤተመጻሕፍት ዓይነቶች፦ የትምህርት ቤት፣ የኮሌጅ እና የዩኒቨርሲቲ ቤተመጻሕፍት አደረጃጀት ሥርዓት፣ ልዩ ልዩ የቤተመጻሕፍት ዘርፎች፦ በአንድ የትምህርት ሙያ ላይ ብቻ የሚያተኩሩ ልዩ ቤተመጻሕፍት (Special Libraries)፣ አገር አቀፍ ቤተመጻሕፍት፣ የሕዝብ (Public) እና የኮሚኒቲ ቤተመጻሕፍት ምንነትና አሠራር በዝርዝር ተዳስሰዋል። በመርሃ-ግብሩ ማጠቃለያ የ«ነገ ሌላ ቀን ነው» ተቋም አባላት የአብርሆት ቤተመጻሕፍትን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴዎችን በአካል በመዘዋወር ጎብኝተዋል።

Photos from Abrehot Library's post 25/05/2026

ከሰዎች ጋር የመኖር ጥበብ እና ከሰው መጠበቅ

በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዐት መግቢያ በፊት በሚዘጋጀው ወርቃማው ሰኞ የሰራተኞች መርሀ ግብር ላይ ``ከሰዎች ጋር የመኖር ጥበብ እና ከሰው መጠበቅ’’ በሚል ርዕስ የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ሰራተኛ የሆኑት ወ/ሪት ቅድስት አራጋው ለሰራተኛው ግንቦት 17/2018 ቀን ማብራሪያ አድርገዋል፡፡ በገለጻቸውም ከሰው ጋር የመኖር ጥበብ ማለት ዕውቀትን፣ የስሜት ብልህነትን (EQ) እና ማኅበራዊ ግንኙነትን (SQ) በትክክል በመጠቀም ከሰዎች ጋር ሰላማዊ ሕይወት የመኖር ሥርዓት እንደሆነ አስረድተዋል። ይህ ጥበብ ሰራተኞች ግጭቶችን በሰላም እንዲፈቱ እና ሕይወትን በሚዛናዊነት እንዲመሩ ያደርጋል።
በተጨማሪም ከሰዎች ከመጠን በላይ መጠበቅ (Expectation) ማለት «ያልተነገረ ስምምነት» መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ልማድ ለሥር ብስጭት፣ ጭንቀትና ለራስ ዋጋ መቀነስ እንደሚዳርግ አብራርተዋል። በመሆኑም በመጠበቅ የሚመጣን መጎዳት ለመቀነስ መፍትሄው የራስን ዋጋ መረዳት፣ የሰዎችን ውስንነት መቀበል እና «ከሰዎች ምን አገኛለሁ?» ከሚል ይልቅ «እኔ ለራሴ ምን እሰጣለሁ?» በሚለው መርህ ላይ ማተኮር እንደሆነ በማጠቃለያው አስገንዝበዋል። በጥበብና ከሰው ባለመጠበቅ ለሰው መልካም በማሰብ ደስተኛ የሥራና የኑሮ ግንኙነት እንዲኖረን እንደሚያደርግ በመግለፅ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

መልካም የስራ ሳምንት!

Want your organization to be the top-listed Government Service in Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Addis Ababa
Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 00:00