WolloPedia
02/05/2026
👉የድሬዳዋ ነዋሪ የነበሩት የልጅ እያሱ ልጅ
በምስሉ ላይ የሚታዩት ልጅ ምኒልክ ይባላሉ። ልጅ ምኒልክ - የልጅ እያሱ ልጅ ሲሆኑ ለአፄ ምኒልክ ደግሞ የልጅ ልጅ ልጅ ናቸው።
እናታቸው ፋጡማ መሐመድ አቡበከር ባሻ ይባሉ ነበረ። የፋጡማ አባት አቡበከር መሐመድ የታጁራ ሱልጣኔት የ"ነጋድራስ መሀመድ" ልጅ ሲሆኑ ይኸም በዘር ሀረጋቸው በዘይላ ሀሶባ ውስጥ ካለው የአፋር ኦባካርቶ የሚመዘዝ ያደርገዋል።
ልጅ ምኒልክ በአፄ ኃይለ ሥላሴ የሥልጣን ዘመን ብዙውን ዕድሜያቸው የቁም እስረኛ ሆነው ነው ያሳለፉት። ድሬዳዋ ውስጥ የመኖሪያ ቤታቸው ድልጮራ ሆስፒታል አካባቢ ነበር።
✍️Jemal abdulaziz
👉Calvert Advert ደግሞ ይህን ትውስታውን አካፍሎናል 👇👇👇
ምኒልክ እያሱ ድሬዳዋ ከዚራ ወደ
ኮካኮላ መታጠፊያ ጫፍ ላይ ያለ አሁን ደሳለኝ ካፌ እና ፋርማሲ የሆነው (ጊቢው ለሁለት ተከፍሎ) ማለት ነው ምኒልክ እያሱ ያረፉትም በ80ዎቹ መጀመሪያ ላይ ይመስለኛል።
ልጅ እያሱ አንድ ሐኪም መርፌ ሲወጋቸው አረፉ ሲባል ወሬው በሰፊው ሲወራ ልጆች ሆነን እሰማ ነበር።
የምማርበት ከቤታቸው ፊት ለፊት ከዚራ ት/ቤት ስለነበረ ልጅ ልጃቸው በእናቷ የአረብ ዝርያ ያላት አንድ በቅርብ የማውቀው ተስቲ(ደስታ) ማለት ነው በአማርኛ እሱን በ90ዎቹ ላይ አግብታ ለገሃሬ አካባቢ መኖሯን ትዝ ይለኛል።
01/05/2026
ህገ ወጥ ታሪፍ ለመጠቆም የስልክ አድራሻወች ከዚህ በታች ተቀምጠዋል
ህገ ወጥ ታሪፍ ጭማሪን ለመከላከልና የተጓዦችን መብት ለማስጠበቅ ህብረተሰቡ ከትራንስፖርት ታሪፍ ጋር የተያያዙ ህገወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልበስልክ ጥቆማእንዲያቀርብ የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ወንጀል መከላከል ምክትልመምሪያ የመንግድ ትራፊክ ደህንነት ዋና ክፍል ሃላፊ ዋ/ኢ/ር ከተማው ታደሰ ገልጿል።
ህብረተሰቡ በየአካባቢው የሚፈጸሙ ህገወጥ የታሪፍ ጭማሪዎችን፣ የተሳፋሪዎች እንግልትን እና ሌሎች ከመጓጓዣ አገልግሎት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ህጋዊ ሥርዓት እንዲከበር የድርሻውን እንዲወጣ ተጠይቋል። ማህበረስቡ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስልኮች ጥቆማ እንዲስጥ ተጠቁሟል።
➥መምሪያ
📞0973033596
📞0914715565
📞0914057274
📞0910964989
➥1ኛ ዋና ፖሊሰ ጣቢያ 📞0914710725
➥2ኛ ዋና ፖሊሰ ጣቢያ 📞0911366770
➥3ኛ ዋና ፖሊሰ ጣቢያ 📞0920770227
➥4ኛ ዋና ፖሊሰ ጣቢያ 📞0931623410
➥5ኛ ዋና ፖሊሰ ጣቢያ 📞0914604929
➥የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ መረጃ ፡- 033-111-7748
➲ 1ኛ ጣቢያ 033 111 11 07
➲ 2ኛ ጣቢያ 033 111 16 01
➲ 3ኛ ጣቢያ 033 111 10 11
➲ 4ኛ ጣቢያ 033 111 51 19
➲ 5ኛ ጣቢያ 033 312 36 69
በእነዚህ ቁጥሮች በመደዉል መረጃ እና ጥቆማ መሠጠት ይቻላሉ።
የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ወንጀል መከላከል ምክትል መምሪያ የመንግድ ትራፊክ ደህንነት ዋና ክፍልየሚቀርቡ ጥቆማዎች በሚስጥር እንደሚያዙ እና በተሰጠው መረጃ መሰረት ፈጣን የቁጥጥርና የህግ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጿል።
(ደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያህዝብ ግንኙነት)
ደሴ _ማያዚያ 23/2018ዓ,ም
12/03/2026
የቦረና አውራጃ አፍለኞች በ/ቦ/ከ/ት
"""""""""""""""''''''""''"'"''''''''"""""""'"'''''''''''
ከቀለም ጋር ግብግብ ገጥመን ትኩስና የአፍላነት ዘመናችንን ያሳለፍንበት ብዙዎች ነን ። በዘመኑ እዚያ ተምረን ከተንጠባጠብነው በስተቀር የአያሌ ግምቱ ምህራን መፍለቂያነቱን በተጨባጭ ያስመሰከረ አንጋፋና ታዋቂ ነው ። ቦረና ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህር ቤት ። ቦ/ ከ / ት !!
የቦረና ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በትምህርት ፣ በህክምና ፣ በግብርና ፣ በኢኮኖሚ ፣ በህግ ፣ በፍልስፍና ፣ በጥበብ ፣ በፖለቲካውና በሌሎችም ዘርፎች ጫፍ የነኩ ዕወቅ ምህራንን የሰራ በስስት የምንመለከተው አንድ ለእናቱ የእውቀት አድባራችን ነበረ ።
ከ4ቱም ወረዳዎች በመሰባሰብ በፍልቅልቋ መካነሰላም ከተማ ሃይስኩል ላይ ጣፋጭ የትምህርት ጊዚያችሁን ያሳለፋችሁ ሁሉ በያላችሁበት ሰላምታየ ይድረስልኝ ብያለሁ ።
የህይወት እጣ ፈንታችን ሆነና ከተለያየን ዘመናትን ያስከነዳን ቢሆንም በቦረና ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያሳለፍነው አይረሴ የአፍላነት ዘመን ትዝታ አብሯችሁ እንደሚገኝ ግን አምናለሁ ።
" ነገርን _ ነገር ያነሳዋል እንድሉ " ዛሬ ቦረና ወረዳ መካነሰላም ከተማ መጥቼ የሃይስኩል ትዝታዬ እንደገና ተቀሰቀሰብኝና በዚያ ዘመን ስሜት ላይ ሆኘ ይሄን ፃፍኩኝ ።
በትዝታ ፈረስ በናፍቆት ባቡር
መጣሁ ስገሰግስ ቦረና ምድር ።
እንደት ነው ቦረና ዙሪያ ገመገሙ
የነሸግየ አገር የነአይጠገቡ ።
በል ! በል ! በል ! በል አለኝ ።......
እናም ጥቂት ጓደኞቸን በትዝታ ባቡር አሳፍሬ ወደ ሃይስኩል ዘመናችን ስጥም ብየ ገባሁ ። ወደዚያ ጣፋጭ ጊዜ ። ወደዚያ ወደ ገናናው ቦረና አውራጃ ትምህርት ቤት ነጎድኩኝ ።
የኛ ትዝታ በአብዛኛው ከዚያ ይጀምራል ። ትዝታችን የቀድሞውን ከአሁኑ ጋር የሚያስተያይ የዘመን መደላድልና የሁኔታ ነፀብራቅ ነው ። የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ፣ የአንድነትና የጋራ የዘመን ላይ ድልድይ !!
እኛ ማለትም ----- ሰለሞን ፣ በለጠ ፣ ብርሃኑ ፣ ተስፋዬ ፣ ጌታቸው ፣ ዘበናይ፣ ገለታ ፣ አማረች ፣ ዋጋየ ፣ አለሙና መሐመድ በአንድ ሌማት የበላን ፣ በአንድ ኩራዝ ያጠናን ፣ የአንድ ሃይስኩል እና የአንድ ጀመዓ ቅምጥሎች ነን ።
አስተሳሰባችንም - አመለካከታችንም አንድ የነበረ በአካልና በመንፈስ የተዋሃድን ሽቅርቅሮች እኛ ነን ።
ውበት ፣ ቁንጅና ፣ ለዛ ፣ ዝነጣ ፣ ጀግንነት ፣ እኛ ላይ ብቻ የተፈጠረ እስኪመስለን ድረስ የምንጠራራ የቦረና ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አፍለኞች ነበርን ኮ ።
ያይኔ አበባነሽን የዘመርን ፣ እሸት በላሁኝን ያቀነቀንን፣ የፊክሽን መጽሃፍ በጉያችን ይዘን የዞርን ፣ ከስመመን - የአቤልን ፣
ከፍቅር እስከ መቃብር የሰብለን - ገጸ ባህሪ ለመላበስ የምንፍጨረጨር ፣ እንደ ጉዱ ካሳም የሚቃጣን ልበ ተራሮች ነበርን ።
እስካርቭ ከአንገታችን የማይጠፋ ፣ በአለባበስ ፣ በአረማመድ ፣ በአነጋገር ፣ ልክ እንደ ቲቸር አረጋ ለመሸለል ነጠር - ነጠር የሚያደርገን የመካነሰላም ወላፈኖች ነበርን ።
አንዳንዶቻችንም በተለየ ሁኔታ ትምህርት አቀባበል ፣ ጨዋታ አዋቂነትና ፀባየ ሸጋነት መለያችን የሆነ_ መረብ ኳስ ፣ ቅርጫት ኳስ ፣ እግር ኳስ ፣ ቴንስ ሲሉን ጨርቃችንን ጥለን የምናብድ ስፖርት አምላኩና ጆላዮችም ነበርን ።
የትምህርት አይነቱን ሁላ በእኩል የሚያስተናግዱ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ፣ የኋላ ኋላም ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገው ትተው ወደ ሃይማኖት የገቡና በዘርፉ ሊቅ የሆኑ ምርጦችም አሉን ።
በጥበብ ዘርፍም ጥግ ድረስ እንደሚደርሱ ምልክት የሚታይባቸው ጀለሶችም ነበሩን ። እውነትም ታዲያ ዛሬ በየመድረኩ የነገሱ ፣ በዝናና በገንዘብ የናጠጡ እንደፈርጥ አንፀባራቂ ሰወችም ሆነዋል ።
የህይወትን ጥሪ ተቀብለው በአሁኑ ሰዓት በአውሮፓ ፣ በአሜሪካና በአረብ አገሮች ውስጥ ኑሯቸውን ያደረጉም ለሽ ናቸው ።
እኛም በመንደራችን ውስጥ ሆነን ይሄን fb ላይ እንቸከችካለን ።
ሰለሞን ግን እስካሁን አልተለየኝም ። ሁሌም ሰሌ እያልኩነው የምጠራው ። በጨዋታችን መሃል የሃይስኩል ትዝታችንን መለስ እያልን እንቃኘዋለን ።
ሰሌ ይሄን ትዝታ እጅግ ይወደዋል ። ያጣጥመዋል ። የዛሬውን ከትናንቱ ጋር እያወሃደ ዘመንን የሚመለከትበት የህይወት ኮምፓሱ አድርጎታል ።
" ሰሌ የአንተን ነገር ወፍ ትልቀመው " ብየ ትዝታችንን ሳነሳበት ፈገግ ማለት ይጀምራል ። ጨዋታ አዋቂ፣ መልከ ቀናና ፣ ለዛ ያለው ልጅ ነው ። አንድ ቀን ግን የነካውን እንጃ የአንድ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ጉድ አድርጎን ያውቃል ።
የሶየ ልጆች የኔን ከንፈር ወዳጂ በክፉ አዩብኝ በሚል አጉል ቅናት ሀጋ ለይተን በሽመል እንድንቀራደድ ፈርዶብናል ። ይሄን ሳነሳበት ከልቡ ይንከተከትና
" አይይይይ..... ፈንቲ የስራሽን ይስጥሽ ። " ይላል ።
ፈንቲ ይማም ሁሌም ተበችሳ በሆነ ቁጥር " ሸጌ የዱላው ለት " የሚለውን የልጃገረዶች ግጥም በዜማ የምታቀነቅንለት የከንፈር ወዳጁ ነች ። ግጥሙ ለሱ ብቻ የተፃፈ ይመስለዋል ።
" አባይ ወድህ ማዶ ቦረና ነው ቤቴ
ማተብና ድንብል ላክልኝ በሞቴ ማተቡም ይቅርብኝ ድንብሉም ይቅርብኝ
ሸጌ የዱላው ለት እንዳትቀርብኝ
ሸጌ የዱላው ለት የቀረህ እንደሆን
እንኳን ከንፈር ወዳጀ ጎረቤትም አንሆን
ትልና ......
" አይኑን በቀጫጭን የተኳኳለው
ጥርሱን ጉራማይሌ የተዋቀረው
ሰለሞን ተሰማ ይላሙ ያለው ። "
የሚለውን ትጨምርለታለች ።
ይሄን - ይሄን ሳስታውሰው ሰሌ የሚሆነውን ያጣል ። " አሁን ሁሉንም ነገር እያነሳህ አደባባይ ባታሰጣው ምን አለ ? " ይለኛል ።
" ሰው የሰራው በጎም ይሁን - ክፉ ነገር የህይወቱ አንድ ክፍል ሆኖ ታሪክ ይመዘገብለታል ። እናም ከሃይስኩል ታሪክህ ትንሽ ቀነጨብኩ ። " እለዋለሁ ።
" ተው - ተው ጋሽቲ ሸጋ ሸጋውን ክተብ " ይልና
ቦረና በተነሳ ቁጥር የሚያሳየውን ደማቅ ፈገግታ ይጨምርበታል ።
እኛ እንደዚህ ነን ። በዘመን እየተሸመን ፣ በጋራ እየተገመድን ፣ እዚህ የደረስን የቅብብሎሽ ልቃቂቶች ። የዚያ ዘመን የቦረና አውራጃ አፍለኞች እኛ እንደዚህ ነን !!
አበቃ !!
ጋሻው መኮንን
ከመካነሰላም ፒያሳ
Klicken Sie hier, um Ihren Gesponserten Eintrag zu erhalten.